6192 በይፋ ተዋወቀ

መጋቢት 29/2015ዓ.ም ከቀኑ በ9 ሰዓት በጋራ ላይ ሆቴል በኢትዩጵያ የመጀመሪያ የሆነው የምግብ ባንክ በመልካም ትውልድ ለአለም በሚባል በጎአድራት ድርጅት የማስተዋወቅ እና የድጋፍ ማድረጊያ ቁጥር 6192 ኦኬ ተዋውቋል፡፡

በዕለቱ ከሌሎች አጋር ድርጅቶች ጋር ከሴንተር ፎር ፋሚሊ ኦርጋናይዜሽን ጋር በህጻናት እና በወጣቶች እንዲሁም ልዩ ፍላጎት ባላቸው ልጆች የምገባ ፕሮግራም እና ሎሌች ድጋፎችን እና ስልጠናዎችን በጋራ በማስተባበር በትብብር ለመስራት የፊርማ ስነስረአት ተደርጎል፡፡

እንዲሁም የመልካም ትውልድ ለአለም በኢትዩጵያ መስራች እና የቦርድ ሰብሳቢ አቶ አክሊሉ መለሰ እንደተናገሩት በቀጣይ በ100የኢትዩጵያ ከተሞች 100 የምግብ ማዕከላት በ1ቢሊየን ብር በማስገንባት ከማህበረሰብ ጅመሮ በከተማ እና በሀገር የምግብ ዋስትና በኢትዩጵያኖች ትብብር እንደሚረጋገጥ ተናግረዋል፡፡

በተጨማሪም የድርጅቱ ማኔጂንግ ዳይሬክተር የሆኑት ወ/ሮ መሰረት ባዩ በተመሳሳይ እያንዳንዱ ኢትጵዩጵያዊ በድጋፍ እና በርብርብ በመሳተፍ ኢትጵዩጵያ ከራሶ አልፋ አለምን የመመገብ አቅም እንዳላት ለማሳየት የተቋቋሞ በጎአድራጎት ድርጅታቸን በቀጣ ከተለያዩ አጋር ድርጅቶች ጋር የተለያዩ የትብብር ስምምነቶች በማድረግ በሀገሪቷ ያለውን እምቅ ሀብት በማውጣት በትብብር እንድንሰራ እና የአጭር ቁጥሩን በመጠቀም ሁሉም ኢትዩጵያዊ ድጋፍ እንድያደርግ ጥሪ አቅርበዋል፡፡

ድርጀቱ ከቋቋመበት የምግብ ባንክ ጎን ለጎን በትምህርት እና ስልጠና በሀገር ውስጥ እና በውጪ ሀገራት አሰልጣኞች በመታገዥ ትውልዱን ከህይወት ክህሎት ጀምሮ የተለያዩ ፕሮፌሽናል ስልጠናዎችን በማሰልጠን ላይ እንዳሉ የድርጅቱ የስልጠና አስተባበሪ የሆኑት አቶ ማቲዩስ ፋንታሁን ገልጸዋል ፡፡

በመጨረሻም የሴንተር ፎር ፋሚሊ ኦርጋናይዠየሽን መስራች የሆኑት አቶ ተፈሪ በቀጣይ በትብብር ለምንሰራቸው ስራዎች ውጤታማ እንደሚሆኑ በመግልጽ ሁሉም ኢትዩጵያዊ አጭር ቁጥሩን በመጠቀም ድጋፍ እንዲያደረግ ጥር አስተላልፈዋል፡፡

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *